ከዕደ-ጥበባት ኢንዱስትሪ የሚገኘውን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ማላቅ ይገባል

AMN – ነሐሴ 22/ 2018 ዓ.ም

የዕደ-ጥበባት ኢንዱስትሪውን በማጎልበት ከዘርፉ የሚገኙ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነትን ማላቅ እንደሚገባ ተገለጸ።

የአዲስ አበባ ባህልና ኪነ-ጥበብ ቢሮ ይህን የማህበረሰብ መገለጫ የሆነውን የዕደ-ጥበብ ኢንዱስትሪ ማሳደግ በሚቻልበት አግባብ ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ተወያይቷል።

በመድረኩ የቢሮው ምክትል ኃለፊ አዲሱ ሻንቆ (ዶ/ር) እንደገለጹት፤ አዲስ አበባ ብዝሀ ማንነት ያለባት ከተማ በመሆኗ በርካታ የዕደ-ጥብብ ስራዎች ይገኛሉ፡፡

እነዚህ የዕደ-ጥበብ ስራዎች ዘመኑን በዋጀ አግባብ እንዲሰሩ በማስቻል ኢትዮጵያን እንዲያስተዋውቁ እና ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታን እንዲያበረክቱ እየተሰራ ነው ብለዋል።

አዲስ አበባ በከተማ ልማት ግንባታ ውስጥ ለዕደ-ጥብበ ውጤቶች ልዩ ትኩረት መስጠቷ ለዘርፉ ከፍተኛ መነቃቃትን ስለመፍጠሩም ኃላፊው ተናግረዋል።

የመዲናዋ የቱሪዝም መዳረሻነት እያደገ መምጣቱ ከፍተኛ መነቃቃት ፈጥሯል ያሉት ደግሞ በመድረኩ የተሳተፉ የዕደ-ጥበባት በለሙያዎች ናቸው፡፡

የዘርፉ ባለሙያዎች ዘመኑን በዋጀ መልኩ ምርቶቻቻውን ማምረትና ተደራሽ ማድረግ አለባቸው ብለዋል።

የዕደ-ጥበብ ኢንዱስትሪውን በተገቢ ሁኔታ ማስተዋወቅን ጨምሮ በዘርፉ የሚታዩ ማነቆዎች ለመፍታት በቅንጅት ሊሰራ እንደሚገባ ከመድረኩ ተሳታፊዎች ተነስቷል።

በሄኖክ ዘነ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review