የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ተጠባቂ ጨዋታዎች

AMN – ነሐሴ 23/2018 ዓ.ም

በሁለተኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ዛሬ አራት ጨዋታዎች ሲደረጉ ፣ ሊቨርፑል ከኖቲንግሃም ፎረስት እና ቶተንሃም ከኒውካስል የሚያደርጉት ጨዋታዎች ይጠበቃሉ፡፡

ሊቨርፑል ከኖቲንግሃም ፎረስት የሚያደርጉት ጨዋታ ከቀኑ 8 ሰዓት ከ30 በአንፊልድ ስታዲየም የሚካሄድ ይሆናል፡፡

በመጀመሪያ ሳምንት መርሃ ግብር ሊቨርፑል ከኒውካስል ዩናይትድ ጋር ነጥብ ሲጋራ ኖቲንግሃም ፎረስት ደግሞ በሊድስ ዩናይትድ መሸነፉ የሚታወስ ነው፡፡

ቶተንሃም ሆትስፐር ከኒውካስል ዩናይትድ የሚያደርጉት ጨዋታ ደግሞ ምሽት 1 ሰዓት ከ30 ይደረጋል፡፡

ቦርንማውዝ ከኤቨርተን እና ኮቨንትሪ ከሀል ሲቲ 11 ሰዓት ላይ የሚያደርጓቸው ግጥሚያዎች ሌሎች የሁለተኛ ሳምንት መርሐ ግብሮች ናቸው፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review