AMN – ነሐሴ 23/2018 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ቴአትር ቤቶች አስተዳደር ድርጅት ባልቻ አባ ነፍሶ ቴአትርን በወሊሶ ከተማ አሳይቷል።
በጀግናው ደጃዝማች ባልቻ ሳፎ የጀግንነት ታሪክ ላይ የተሰራው ባልቻ አባ ነፍሶ ቴአትር በትውልድ ስፍራቸው ወሊሶ ከተማ በልዩ ዝግጅት ተመርቋል።

በብርሃኑ ዘሪሁን ተደርሶ በዶ/ር ተሻለ አሰፋ የተዘጋጀውን ባልቻ አባ ነፍሶ ታሪካዊ ቴአትርን ፣ የአዲስ አበባ ቴአትር ቤቶች አስተዳደር ድርጅት ከወሊሶ ከተማ አስተዳደር እና ከደጃዝማች ባልቻ ሳፎ ቤተሰብ ከወ/ሮ ዝምታወርቅ ነጋሽ ጋር በመተባበር ነው ያስመረቀው፡፡

የወሊሶ ከተማ አስተዳደር የባልቻ አባ ነፍሶ ቴአትር አባላትን በልዩ ሁኔታ አቀባበል በማድረግ አክብሮቱን አሳይቷል፡፡
የአዲስ አበባ ቴአትር ቤቶች አስተዳደር ድርጅት ከወሊሶ ከተማ አስተዳደር የፈረስ ስጦታ የተበረከተለት ሲሆን ፣ የአዲስ አበባ ቴአትር ቤቶች አስተዳደር ድርጅትም የጀግንነት መልክት የሆነውን ጋሻና ጦር ለከተማ አስረዳደሩ ከንቲባ አቶ ገመቹ አረዳ በስጦታ ማበርከቱን ከድርጅቱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡