AMN – ነሐሴ 23/2018 ዓ.ም

የሴካፋ ዞን የካፍ ሻምፒዮንስ ሊግ ማጣሪያ የግማሽ ፍፃሜ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከካዌምፔ ሙስሊም ሌዲስ ጋር ያደረገዉን ጨዋታ 3 ለ 0 ተሸንፎ ወደ ፍፃሜ ሳያልፍ ቀርቷል::
ለካዌምፔ ሙስሊም ሌዲስ የማሸነፊያ ግቦችን ጆቪያ ናካጎሎ፣ ትእግስት አዳነ (በራሷ ላይ) እና አግኔስ ናቡኬንያ ከመረብ አሳርፈዋል::
ዉጤቱን ተከትሎ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ወደ ፍጻሜ ሳያልፍ ቀርቷል።
ክለቡ በመድረኩ ሶስት ጨዋታ አድርጎ አንዱን ብቻ ሲያሸንፍ በሁለቱ ተሸንፏል::
በአዲሱ መንገሻ