ተኪ ምርት ከማምረት እስከ ውጭ ምንዛሬ ግኝት የአዲስ አበባ አምራች ኢንዱስትሪዎች ስኬት

You are currently viewing ተኪ ምርት ከማምረት እስከ ውጭ ምንዛሬ ግኝት የአዲስ አበባ አምራች ኢንዱስትሪዎች ስኬት

AMN- ጳጉሜን 1/2018 ዓ.ም

የበርካታ አምራች ኢንዱስትሪ መገኛ በሆነችው አዲስ አበባ ከተማ ዘርፉን ለማሳደግ በተከናወኑ ሥራዎች ከሸማችነት ወደ አምራችነት የሚያሸጋግሩ ስኬቶች ተመዝግበዋል።

በከተማዋ ለአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉ በተሰጠው ትኩረት ከውጭ የሚገባን ምርት በሀገር ውስጥ በማምረት የውጭ ምንዛሬን ማዳን እየተቻለ ነው።

በመዲናዋ አጠቃላይ ጥቃቅን ኢንዱስትሪዎችን ሳይጨምር ከ300 በላይ መካከለኛ ከፍተኛ ኢንዱስትሪዎች የተለያዩ ምርቶችን እያመረቱ ይገኛሉ፡፡

አምራቾች ውጤታማ እንዲሆኑ የሚያጋጥማቸውን ችግር በመፍታት ምርታማነታቸውን እንዲያሳድጉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተለያዩ ድጋፎችን እያደረገ ይገኛል፡፡

አምራቾች የሚያነሷቸው የኤሌክትሪክ ፣የፋይናንስ እና የመሰረተ ልማት አቅርቦች ችግሮች በፍጥነት መፍትሄ እንዲያገኙ ተደርጓል።

ባለፉት አመታት ልዩ ትኩረት የተሰጠው የኢትዮጵያ/አዲስ አበባ ታምርት ንቅናቄ የአምራቾችን የሀገር ውስጥ የገበያ ድርሻ አሳድጓል፡፡

አዲስ አበባ የኢንዱስትሪ፣ የንግድ እና የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴዎች ዋና መሠረት በመሆን እያገለገለች ትገኛለች።

አዲስ አበባ ለአገር ውስጥ እና ለውጭ ባለሀብቶች ምቹ የሆነ የንግድ ከባቢያዊ ሁኔታ በመፍጠር በርካታ የማኑፋክቸሪንግ፣ የአገልግሎት እና የቴክኖሎጂ ኢንዱስትሪዎችን እየሳበችም ትገኛለች፡፡

በከተማዋ ሰፊ የሰው ሃይል መገኘቱ ደግሞ ለአምራች ኢንዱስትሪው ውጤታማነት ትልቅ ድርሻ ያለው ሲሆን የትራንስፖርት፣ የኤሌክትሪክ ሃኃይል እንዲሁም የቴክኖሎጂ መስፋፋት የኢንዱስትሪዎችን ምርታማነት ከፍ አድርጎታል።

አምራች ኢንዱስትሪዎች ተኪ ምርቶችን ከማምረት ባለፈ በውጭ ምንዛሬ ግኝት፣ ለዜጎች የሥራ እድል ፈጠራና ለሃገር ኢኮኖሚ ግንባታ ጉልህ ሚና እየተጫወቱ ነው፡፡

የሻምበል ምህረት

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review