ከሀገራዊ ምክክር ጉባኤው የተገኙ ምክረ-ሃሳቦች እየተደራጁ ነው -የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን

AMN-ጳጉሜን 2 /2018 ዓ.ም

ኮሚሽኑ ከሀገራዊ ምክክር ጉባኤው የተገኙ ምክረ-ሃሳቦችን በየፈርጁ በማደራጀት ላይ እንደሚገኝ ገልጿል።

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከሐምሌ 01 ቀን – ነሐሴ 16 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ የሀገራዊ ምክክር ጉባኤውን ሲያስተባብር መቆየቱ የሚታወስ ነው፡፡

በዚህ ሂደት ኮሚሽኑ በርካታ ሀገራዊ ፋይዳ ያላቸውን ምክረ-ሃሳቦች ማሰባሰብ የቻለ ሲሆን ይህም ኢትዮጵያዊያን በሀገራቸው ጉዳይ ላይ ለመመካከር ያሳዩት ቁርጠኝነት ውጤት ነው፡፡

ኮሚሽኑ በአዋጅ ቁጥር 1265/2014 አንቀፅ 9 (10፣ 11፣ 12) በተሰጠው ሥልጣንና ኃላፊነት መሠረት

📌የሀገራዊ ምክክር ጉባዔ አጀንዳዎችን፣ የምክክሮቹን ሂደት፣ በምክክሮቹ የተገኙ ምክረ-ሃሳቦችን እንዲሁም ምክረ- ሃሳቦቹ በተግባር ላይ ሊውሉ የሚችሉበትን ሥልት የሚገልጽ ሰነድ በማዘጋጀት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ ለአስፈጻሚ አካሉ እና ለሌሎች የሚመለከታቸዉ የመንግስት አካላት አቅርቦ፤ ለሕዝብም ይፋ እንደሚያደርግ፤

📌 መንግሥት ከሀገራዊ ውይይቶች የሚገኙ ምክረ-ሃሳቦችን በተግባር ላይ ለማዋል እንዲችል ግልፅ እና ተጨባጭ የሆነ ዕቅድ እንዲዘጋጅ አስፈላጊውን እገዛ እንደሚያደርግ፤ እንዲሁም

📌 የምክረ-ሃሳቦቹን አፈፃፀም መከታተል የሚያስችል ሥርዓት እንደሚዘረጋ በአዋጁ ተደንግጓል፡፡

ይህንን መነሻ በማድረግ ኮሚሽኑ፦

📌በአሁኑ ሰዓት ከሀገራዊ ምክክር ጉባኤው የተገኙ ምክረ-ሃሳቦችን በየፈርጁ በማደራጀት ላይ ይገኛል፤

📌በቀጣይ ምክረ-ሃሳቦቹን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያቀርባል፤

📌በመቀጠልም ምክረ-ሃሳቦቹን አግባብነት ባለው መንገድ ለሕዝብ ይፋ ያደርጋል፤

📌 በመጨረሻም ምክረ-ሃሳቦቹን ለአስፈፃሚ በማቅረብ ተፈፃሚነታቸውን ይከታተላል

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review