AMN- ጳጉሜን 5/2018 ዓ.ም

የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ ለአዲስ ዓመት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
ፕሬዝዳንቱ በመልዕክታቸው “እንኳን ለ2019 አዲስ ዓመት በሰላም አደረሳችሁ!”ያሉ ሲሆን አዲሱ ዓመት በይቅርታና በምክክር የጀመረውን ብሩህ ጉዞ የምናጸናበት፣ ኢትዮጵያን እያስቀደምን በቀጥተኛው ርቱዕ መንገድ የምንጓዝበት የሰላም፣የፍቅር፣የአንድነትና የስኬት ዘመን እንዲሆን ተመኝተዋል።