ልቅና አምባው የአልቲሜት ቻምፒየንሺፕ የ5000 ሜትር አሸናፊ ሆነች

You are currently viewing ልቅና አምባው የአልቲሜት ቻምፒየንሺፕ የ5000 ሜትር አሸናፊ ሆነች

AMN-መስከረም 3/2019 ዓ.ም

ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ልቅና አምባው የአልቲሜት ቻምፒየን ሺፕ የ5000 ሜትር አሸናፊ ሆናለች።

አትሌቷ ርቀቱን ለማጠናቀቅ 14:30.36 የሆነ ሰዓት ፈጅቶባታል። ፋንታዬ በላይነህ ፣ ፍሬወይኒ ሀይሉ እና አለሽኝ ባወቅ በቅደም ተከትል ከ2-5 ያለውን ደረጃ ይዘው አጠናቀዋል።

አትሌት ልቅና ወርልድ አትሌቲክስ ለመጀመሪያ ጊዜ ባካሄደው የአልቲሜት ቻምፒየን ሺፕ ላይ ድል ያደረገች የመጀመሪያዋ ኢትዮጵያዊት ሆናለች።

የውድድሩ አሸናፊ በመሆኗም 150 ሺየአሜሪካ ዶላር ተሸላሚ ሆናለች።

በሸዋንግዛው ግርማ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review