ብዝሃነት – የኢትዮጵያ የህብረ-ብሄራዊ አንድነት መገለጫ

You are currently viewing ብዝሃነት – የኢትዮጵያ የህብረ-ብሄራዊ አንድነት መገለጫ

AMN-መስከረም 14 /2019 ዓ.ም

ብዝሃነት የኢትዮጵያ ህብረ-ብሄራዊነት፣ የሀገሪቱ የጥንካሬና የስልጣኔ መሰረት ነው።

የቋንቋ፣ የባህል፣ የእምነት ብዝሃነት እና የፓን-አፍሪካኒዝም ማዕከል የሆነችው ኢትዮጵያ የበለጸገች ሀገር ለመሆን እየተጋች ትገኛለች፡፡

ኢትዮጵያ የበርካታ ህዝቦች፣ ቋንቋዎች፣ ባህሎች እና እምነቶች መገኛ ብቻ ሳትሆን የምስራቅ አፍሪካ የጂኦ-ፖለቲካ ማዕከልም ነች።

የኢትዮጵያ ታላቅነት የሚመነጨው ከጂኦግራፊያዊ ስፋቷ ሳይሆን ልዩነትን አቀናጅቶ በመያዝ በህብረ-ብሄራዊነት ማዕቀፍ ውስጥ ከቀጠለው የጋራ ህልውና ነው።

ህብረ-ብሄራዊነት የተለያዩ የማንነት ባለቤት የሆኑ ማህበረሰቦች በዕኩልነት፣ በመከባበር እና በጋራ ጥቅም ላይ ተመስርተው የሚኖሩበት ማህበራዊና ፖለቲካዊ እውነታ ነው።

ከጥንካሬዋ መሰረቶች መካካል የባህልና የቋንቋ ብዝሃነት አንዱ ሲሆን ይህም ከስልጣኔ ማህደር ጀምሮ የበርካታ ቋንቋዎችና ባህላዊ እሴቶች መገኛ መሆኗን ያሳያል።

የታሪክ አብሮነታችን ሌላው ለዘመናት የዘለቀው አብሮ መኖር፣ በውጭ ወረራዎች ጊዜ የተደረገው የጋራ ተጋድሎ የሃገሪቱን ህዝቦች በታሪክ ሰንሰለት አቆራኝቷቸዋል።

ብዝሃነት ይበልጥ እንዲጠናከር የሁሉም ዜጎች የባለቤትነት ስሜት፣ ፍትሃዊ ተጠቃሚነት እና መብቶች መጠበቅ ትልቅ አስተዋጽኦ አለዉ።

በዚህ ረገድ ሀገሪቱ ያላት ሰፊ አቅም ጎልቶ እንዲወጣ የሁሉም የጋራ ኃላፊነት እና ተሳትፎ ወሳኝ ነው፡፡

በፍሬሕይወት ብርሃኑ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review