የመስቀል ደመራ በዓልን የህዝብን የወል እሴቶች በሚያጎላ መልኩ ማክበር ይገባል

You are currently viewing የመስቀል ደመራ በዓልን የህዝብን የወል እሴቶች በሚያጎላ መልኩ ማክበር ይገባል

AMN- መስከረም 15/2019 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ ባህልና ኪነ-ጥበብ ቢሮ የመስቀል ደመራ በዓልን አስመልክቶ ሲምፖዚየም አካሂዷል።

የሲምፖዚየም መድረኩ የመስቀል ደመራ በዓልን ሀገራዊ መግባባትን በሚያጎለብትና የህዝብን የወል እሴት በሚያጎላ መልኩ ማክበር በሚቻልበት አግባብ ላይ ለመምከር ያለመ ነው፡፡

የአዲስ አበባ ባህልና ኪነ-ጥበብ ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አዲሱ ሻንቆ (ዶ/ር)፤ በዓሉ ሐይማኖታዊ ትውፊቱንና ማህበራዊ እሴቱን ጠብቆ እንዲከበርና ለቀጣይ ትውልድ እንዲተላለፍ ማስቻል የሲምፖዚየሙ አላማ መሆኑንም ተናግረዋል።

በዓሉ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታውን በሚያልቅ መልኩ ለማክበር ዝግጅት ስለመደረጉም አንስተዋል፡፡

የመስቀል ደመራ በዓል ከሐይማኖታዊ ትውፊቱና ማህበራዊ እሴቱ ባሻገር የሀገርን ገጽታ በመገንባት ሂደት የላቀ ሚና እንደሚጨወትም ተመላክቷል።

በዓለም ቅርስነት የተመዘገቡ የአደባባይ በዓላት ከህዝቦች አንድነት ከማጠናከር እና ከቱሪዝም ዘርፉ እድገት ባሻገር ለኢንዱስትሪ ዘርፍ ግብዓት በሚሆኑበት አግባብ ማክበር ይገባልም ተብሏል።

በዓሉ ሐይማኖታዊና ታሪካዊ እሴቱ ተጠብቆ በስኬት እንዲከበር ሁሉም የበኩሉን ኃላፊነት እንዲወጣ ጥሪ ቀርቧል።

በሔኖክ ዘነበ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review