AMN- መስከረም 15/2019 ዓ.ም
መስከረም ወር የአዲስ ዓመት መጀመሪያ ብቻ ሳይሆን፣ ኢትዮጵያውያን ማህበራዊ ትስስራቸውን የሚያጠናክሩባቸው፣ የባህልና የታሪክ መገለጫዎቻቸውን ለዓለም የሚያሳዩባቸው ታላላቅ ህዝባዊ በዓላት የሚከበሩበት ወር ነው።
በዚህ ልዩ ወር አዲስ አበባ በአዳዲስ ፓርኮች፣ በተስተካከሉ ኮሪደሮች ፣ በአደይ አበባ እና በለመለሙ አረንጓዴ ስፍራዎች ተውባ እንግዶችን በማስተናገድ የቱሪዝም ማዕከልነቷን ታጠናክራለች።
የመስቀል ደመራ በዓል በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች የሚታደሙበት በድምቀት የሚከበር የፍቅር፣ የሰላም እና የአብሮነት መገለጫ የሆነ አለም አቀፍ ድምቀት ያለው ታላቅ ሐይማታዊ በዓል ነው።
የኦሮሞ ሕዝብ የባህል እሴት መገለጫ የሆነው የኢሬቻ በዓልም በአዲስ አበባ በሆራ ፊንፊኔ የሚከበር ሲሆን የህዝቦችን የአብሮነት፣ የፍቅር እና የሰላም ትስስር ያጠናክራል።
በሚሊዮን የሚቆጠሩ ህዝቦች እና ዓለም አቀፍ ቱሪስቶች የሚሳተፉባቸው እነዚህ በዓላት፣ ከተማዋን የባህል ቱሪዝም ዋና መዳረሻ በማድረግ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴዋን ከፍ እያደረጉ ይገኛሉ፡፡
ከተማዋ የገነባችው ዘመናዊ መሠረተ ልማት ዓለም አቀፍ ቱሪስቶችን በመሳብ አዲስ አበባን የአፍሪካ የቱሪዝም ዋና መዳሻነቷን ከፍ እያደረገው ይገኛል።
በአደይ አበባ ቀለም ታጅቦ፣ እንደ ኢሬቻ እና መስቀል ያሉ ታላላቅ በዓላት ደምቆ የሚፈካው ወርሃ መስከረም በልማት ባጌጠችው አዲስ አበባ እንግዶችን የሚማርክ ልዩ ልዩ ሁነቶች ይከናወኑበታል፡፡
በፍሬሕይወት ብርሀኑ