AMN- መስከረም 15/2019 ዓ.ም
በጃፓን በተካሄደው የጃፓን- አፍሪካ ወጣቶች ፕሮግራም ላይ ተሳታፊ የነበሩና የኢትዮጵያን እንዲሁም የመዲናዋን አዲስ ገፅታ ለማየት አዲስ አበባ የሚገኙ ጃፓናውያን የነጻነት ተምሳሌት የሆነውን የዓድዋ ድል መታሰቢያን ጎብኝተዋል፡፡
በጉብኝቱም በመታሰቢያው የሚገኙ ታሪካዊ ቅርሶችን እና ድሉን የሚዘክሩ የጥበብ ስራዎችን ተመልክተዋል፡፡
ከጉብኝቱ ተሳታፊዎች መካከል ተማሪ ኢኪዳ ናኦኪ፤ በመታሰቢያው ከተመለከታቸው ታሪካዊ ቅርሶች መካከል በጸሐይ አውሮፕላን መገረሙን ነው የገለፀው፡፡
በወቅቱ የነበረውን የኢትዮጵያን የእድገት ሁኔታና ቴክኖሎጂ የሚያሳይ መሆኑንም ገልጿል፡፡
ታሪክ ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲተላለፍ እንዳይዛባ መሰል የታሪክ ሙዚየሞች አስተዋጽኦ የጎላ ነው ማለቱን ከአድዋ ድል መታሰቢያ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡