የኢትዮጵያ የማይቀለበስ ማንነት …

AMN- መስከረም 17/2019 ዓ.ም

የኢትዮጵያ ማንነት በሕዝቧቿ አጥንትና ደም እንዲሁም በዘመናት አብሮነት የተቀረጸ የማይናወጥ ግንብ ነው።

የማይቀለበሰው የኢትዮጵያ ማንነት በየዘመኑ ፈተናዎች ውስጥ እያለፈ ይበልጥ እየጠነከረ እንዲሁም በተጨባጭ መሬት ላይ በሚታዩ እውነታዎች እየተረጋገጠ ይገኛል።

የኢትዮጵያ የነጻነት መንፈስ እና የኩራት ማንነት ከትውልድ ወደ ትውልድ የሚተላለፍ እንጂ በጊዜያዊ ችግሮች ፈጽሞ ሊቀለበስ የሚችል አይደለም።

ይህም በደማቅ ፊደላት፣ በድል አድራጊነት እና በጽናት ማህደሮች የተጻፈ የዘመናት ገድል ሲሆን በዚህም የማይቀለበስ ማንነት ባለቤት መሆኗ እሙን ነው፡፡

በሀገራዊ ጉዳዮች አንድነቱ የተጠናከረ ህዝብ ያላት ኢትዮጵያ ለትውልድ ያስተላለፈችው የነጻነት እና የሉዓላዊነት ተምሳሌትነት በዓለም አቀፍ ደረጃ አርአያም የሚሆን ነው።

እንዲሁም ሀገሪቱ ችግሮቿን በራሷ አቅም የመፍታት ባህልን እያዳበረች መጥታለች። ይህ የማያቋርጥ የህልውና ጽናት የማንነቷ የማይናወጥ መሠረት መሆኑን ያሳያል።

ኢትዮጵያውያን የመከባበር እና የአብሮነት እሴቶች ያሏቸው ሲሆን ይሄም የትኛውንም ከፋፋይ ሃሳብ እንዲያሸንፉ አድርጓቸዋል፡፡

አሁን ላይ ኢትዮጵያ በኢኮኖሚ፣ በቴክኖሎጂ እንዲሁም በታላላቅ የልማት ፕሮጀክቶች አበረታች ውጤቶችን እያስመዘገበች ነው።

እነዚህም በአመራር ቁርጠኝነትና የሀገር ውስጥ አቅምን በማስተባበር የተገኙ ሲሆን የሉዓላዊነቷ እና የዕድገት ጎዳናዋ ወደ ኋላ የማይመለስ መሆኑን በተግባር የሚያሳዩ ናቸው።

በርካታ ብሄር፣ ብሄረሰቦችና ሕዝቦች በአንድነት ተከባብረው የሚኖሩባት ኢትዮጵያ ወደ ላቀ የዕድገት እና የብልጽግና ምዕራፍ እየተሸጋገረችም ትገኛለች።

በልዩነቶች ውስጥ ውበትን ፈጥሮ፣ በሀገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ በአንድነት የቆመው የኢትዮጵያ ሕዝብ ጉዞ ተጠናክሮ መቀጠሉን መረጃዎች ያሳያሉ፡፡

የሻምበል ምህረት

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review