AMN – መስከረም 26/2019 ዓ.ም

የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የመደመር መንግሥት ምስረታ እና ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ዳግም ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው መሰየማቸውን አስመልክቶ የደስታ እና የአጋርነት መልዕክት አስተላልፏል።
ጉባኤው አዲሱ የፌዴራል መንግሥት ምሥረታ በተሳካ ሁኔታ በመካሄዱ እና ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው በድጋሚ በመሾማቸው የተሰማውን ደስታ ገልጿል።
የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ አዲስ ከተመሠረተው የፌዴራል መንግሥት ጋር በመተባበር የጋራ በሆኑ አጀንዳዎች ላይ በሰላም ግንባታ፣ በግጭት መከላከል እና አፈታት፣ የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት በማጠናከር፣ በሃይማኖታዊ ዲፕሎማሲ፣ በማኅበራዊ ጉዳዮች እና በሌሎችም ሀገራዊ አጀንዳዎች ላይ ውጤታማ ሥራ ለመሥራት ከምንጊዜውም በላይ ዝግጁ መሆኑን አስታውቋል።