የናይጄሪያ የመከላከያ አዛዥነት እና ስታፍ ኮሌጅ ተማሪዎች የዓድዋ ድል መታሰቢያን ጎበኙ

AMN-ጥቅምት 4/2019 ዓ.ም

የናይጄሪያ የመከላከያ አዛዥነት እና ስታፍ ኮሌጅ ልዑካን ተማሪዎች የመላው ጥቁር ህዝብ ኩራት የሆነውን የዓድዋ ድል መታሰቢያን ጎብኝተዋል፡፡

ልዑካን ቡድኑ በመታሰቢያው ያደረጉት ትምህርታዊ ጉብኝት፤ በተለይም የድንበር ደህንነትን በተመለከተ ከዓድዋ ድል ትምህርት እንዲያገኙ ያለመ መሆኑን ከዓድዋ ድል መታሰቢያ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ልዑካን ቡድኑ ተዘዋውረው በተመለከቱት ነገር መደሰታቸውን የገለፁ ሲሆን ወደ ሃገራቸው ሲመለሱም በኢትዮጵያ ቆይታቸው ከተማሩት እና ከተረዱት ለሌሎች ግንዛቤ እንደሚፈጥሩ ገልፀዋል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review