መንግሥት የዜጎችን የቤት ፍላጎት ለመመለስ በትኩረት እየሰራ ነው- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

You are currently viewing መንግሥት የዜጎችን የቤት ፍላጎት ለመመለስ በትኩረት እየሰራ ነው- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

AMN- ኅዳር 17/2019 ዓ.ም

መንግሥት የዜጎች የቤት ፍላጎት ምላሽ እንዲያገኝ በትኩረት እየሰራ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።

7ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት 1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤ በመካሄድ ላይ ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ በመስጠት ላይ ይገኛሉ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከዜጎች የቤት ፍላጎት ጋር በተያያዘ ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ማብራሪያ፣ 1.5 ሚሊየን ቤቶችን የመገንባት ውጥን ከጉባ ብስራቶች መካከል አንዱ መሆኑን ጠቅሰዋል።

ከጉባ ብስራት በኋላ የቤቶች ፖሊሲ ዝግጅት፣ የሞርጌጅ ስርዓት፣ የመሬት እና የቴክኖሎጂ ዝግጅት መደረጉን አመልክተዋል።

በአጭር ጊዜ ብዙ ቤቶች ለመገንባት የሚያስችሉ ቴክኖሎጂዎች ከተለያዩ ሀገራት በማስገባት ጥቅም ላይ እየዋሉ እንደሚገኝም ተናግረዋል።

በገጠር እና በከተማ ሰፋፊ የቤት ግንባታዎች እየተደረጉ እንደሚገኝም አንስተዋል፡፡

የቤት ግንባታ ስራው ብዙ ግብአት፣ ልምድ እና እውቀት የሚፈልግ መሆኑን የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ እንደሆነም አብራርተዋል፡፡

ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን ዜጎች ከባንክ ጋር በማስተሳሰር እየሰሩ የተበደሩትን ገንዘብ እንዲከፍሉ የሚያስችል ስርዓት የመዘርጋት ስራም በቅርቡ እንደሚጠናቀቅ አመላክተዋል።

የ1.5 ሚሊየን ቤቶች እቅድ ከባድ መሆኑን ያነሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ነገር ግን ለማሳካት አስፈላጊው ጥረት ሁሉ እየተደረገ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review