AMN – ታኅሣሥ 2/2017 ዓ.ም
ኪነ- ጥበብን ለሀገራዊ አንድነትና ብልፅግና በመጠቀም የአዲስ አበባን ልማት ማረጋገጥ እንደሚገባ በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ከተማ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ ገለጹ፡፡
የጉለሌ ክፍለ ከተማ ”የወል እውነት ለጠንካራ ህብረ-ብሄራዊነት ”በሚል መሪ ሀሳብ የፓርቲውን 5ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ የኪነ- ጥበብ መርሃ-ግብር ተካሂዷል።
ኪነ ጥበብ ሀገራዊ አንድነት እንዲመጣ ፣ ጠላት ሀገርን ሲደፍር ህዝብን በማነቃቃት ጠላትን በማሳፈር ረገድ ትልቅ ሚና እንዳለው ይታወቃል፡፡
በመርሀ-ግብሩ ላይ አሁን ላይ የኢትዮጵያ ፈተና የሆነውን ድህነት ለማስወገድ እና ልማትን ለማረጋገጥ ዜጐች በአንድነት ለሀገራቸው ሰላምና ብልፅግና እንዲነሱ ማድረግ ይገባል ሲሉ አቶ ሞገስ ተናግረዋል፡፡
በመርሃ -ግበሩ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ ባህል’ ኪነ ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ሂሩት ካሳው (ዶ/ር)ን ጨምሮ ሌሎች የከተማ አስተዳደሩ የስራ ኃላፊዎች’ የክፍለ ከተማ አመራሮች እና ነዋሪዎች ተገኝተዋል።
በአንዋር አህመድ