AMN- ሚያዝያ 15/2018 ዓ.ም
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአፍሪካ ሕብረት የሰው ሰራሽ አስተውሎት (Artificial Intelligence) እና የዲጂታል ጤና ዘርፍ መሪ (Champion) ሆነው በመሾማቸው የእንኳን ደስ አሎት መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት መልዕክት፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአፍሪካ ሕብረት የሰው ሰራሽ አስተውሎት (Artificial Intelligence) እና የዲጂታል ጤና ዘርፍ መሪ (Champion) ሆነው በመሾምዎ በራሴና በከተማ አስተዳደሩ ስም እንኳን ደስ አለን ለማለት እወዳለሁ ብለዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትራችን የጥረታቸው ፍሬ በአፍሪካ ደረጃ እውቅና አግኝቶ ለዚህ ሹመት መብቃታቸው ለኢትዮጵያውያን ሁሉ ኩራት ነው ሲሉም አክለዋል።