የምርጫ ካርድ ማውጣት ብቻ በቂ ስላልሆነ መራጩ ህዝብ በምርጫ ቀን ድምፁን እንዲሰጥ ተጠየቀ

You are currently viewing የምርጫ ካርድ ማውጣት ብቻ በቂ ስላልሆነ መራጩ ህዝብ በምርጫ ቀን ድምፁን እንዲሰጥ ተጠየቀ

AMN- ሚያዝያ 21/2018 ዓ.ም

በሰባተኛው ሃገራዊ ምርጫ ለመሳተፍ የምርጫ ካርድ የወሰዱ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች በግንቦት 24ቱ የምርጫ ቀን በንቃት በመሳተፍ ድምፃቸውን እንዲሰጡ የአዲስ አበባ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ጠየቀ።

የጋራ ምክር ቤቱ የሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ የመራጮች ምዝገባ መጠናቀቅን አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል፡፡ የምዝገባ ሂደቱ የተሳለጠና ስኬታማ እንደነበር ያስታወቀው ምክር ቤቱ ነዋሪዎች ድምፃቸው ያለውን ዋጋ በመረዳት ንቁ ተሳትፎ ማድረጋቸውን ገልጿል። ይህም ለዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ያለውን ፍላጎት ያረጋገጠ ስለመሆኑ አስረድቷል።

ምዝገባው በተሳካ ሁኔታ እንዲጠናቀቅ የበኩላቸውን ሃላፊነት ለተወጡ አካላትም ምክር ቤቱ ምስጋናውን አቅርቧል። የመራጮች ምዝገባ መጠናቀቅ ጅማሮ እንጂ ፍፃሜ ስላልሆነ በቀጣዮቹ የምርጫ ሂደቶች ሁሉም አካላት በንቃት እንዲሳተፉ ጠይቋል።

ምክር ቤቱም በተለያዩ ተግባራት ተሳትፎውን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጿል።

በመቅደስ ደምስ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review