AMN ሚያዝያ 24/2018
የመደመር መንግሥት የኢትዮጵያን ብልጽግና እውን ማድረግ የሚያስችል አስተማማኝ መሠረት መጣል መቻሉን በብልጽግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ከተማ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ሞገስ ባልቻ ገለጹ።
የብልጽግና ፓርቲ የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ቅስቀሳ በአዲስ አበባ ስታድየም በመካሄድ ላይ ነው።
አቶ ሞገስ ባልቻ በዚሁ ወቅት ባስተላለፉት መልዕክት፤ ባለፉት አምስት ዓመታት በተከናወኑ ግዙፍ የልማት ሥራዎች የኅብረተሰቡን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ተችሏል ብለዋል።
የመደመር መንግሥት የኢትዮጵያን ብልጽግና እውን ማድረግ የሚያስችል አስተማማኝ መሠረት መጣሉን አስገንዝበዋል።

የሰው ተኮር ሥራዎች የበርካታ ሰዎችን ኑሮ ከመሠረቱ በመቀየር ረገድ ውጤት ማስገኘታቸውን ጠቅሰው፤ የብልጽግና ፓርቲ ለቃሉ የታመነ ለተልዕኮውም የፈጠነ ፓርቲ መሆኑን አስታውቀዋል።
አዲስ አበባን ውብ ከማድረግ አኳያ የተከናወኑ ሥራዎችም ተጨባጭ ለውጥ ማምጣታቸውን ገልጸዋል፡፡
እነዚህን የልማት ሥራዎች አጠናክሮ ለማስቀጠልና የሕዝቡን ተጠቃሚነት ይበልጥ ለማረጋገጥ ኅብረተሰቡ ለብልጽግና ፓርቲ ድምጹን እንዲሰጥ ጠይቀዋል።