የመዲናዋን የልማት ሥራዎች ሲያስተወዋውቅ የቆየው የፎቶ አውደ-ርዕይ ተጠናቀቀ

You are currently viewing የመዲናዋን የልማት ሥራዎች ሲያስተወዋውቅ የቆየው የፎቶ አውደ-ርዕይ ተጠናቀቀ

AMN – ሚያዝያ 28/2018 ዓ.ም

ባለፉት አምስት አመታት በአዲስ አበባ ከተማ የተከናወኑ የልማት ሥራዎችን ለህዝብ ሲያስተዋውቅ የቆየው የፎቶ አውደ-ርዕይ በዛሬው ዕለት ተጠናቋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አሰተዳደር ኮሙኒኬሽን ቢሮ ያዘጋጀው ይህ አውደ-ርዕይ “የእርጅና ገፅታን የገፈፈ ፤ የውበት ፀዳል ያላበሰ” በሚል መሪ ቃል ለ5 ቀናት ሲካሄድ ቆይቷል።

አውደ-ርዕዩ የከተማዋን ሁለገብ ለውጥ የሚያሳዩ በርካታ ምስሎች ለአንባቢያንና ለተመልካች እንዲቀርቡ የተደረገበት ነው።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ሃፍታይ ገብረእግዚአብሔር እንደገለፁት አውደ ርዕዩ ከለውጡ ወዲህ ባሉት አምስት ዓመታት መንግስት ለህዝብ የገባውን ቃል በተግባር መፈጸሙን፣የተመዘገቡ የልማት ውጤቶችንና የከተማዋን ጉዞ በተጨባጭ ለማሳየት ያለመ እንደነበር ተናግረዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ ኮሙኒኬሽን ቢሮ በመንግስትና በህዝብ መካከል ጠንካራ የኮሙኒኬሽን ሥርዓት በመዘርጋት በቂ መረጃ ያለውና በልማት ስራዎች ላይ ንቁ ተሳትፎ የሚያደርግ ማህበረሰብ ለመፍጠር እየሰራ እንደሚገኝም አቶ ሃፍታይ ገብረእግዚአብሔር አክለዉ ገልፀዋል።

አውደ ርዕዩ በመዲናዋ የሚኖሩ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችን ያሳተፈ ሲሆን ጎብኚዎች በመዲናዋ የታዩትን የመሠረተ ልማት ግንባታዎች ፣ የሰው ተኮር ስራዎችንና የከተማ ውበት ስራዎችን በፎቶ አውደ-ርዕይ ሲመለከቱ መሰንበታቸውን የአዲስ አበባ ከተማ ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ ያመላክታል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review