የመሥሪያ ቦታ አቅርቦት የኢኮኖሚ ፍትህን የማስፈን ጉዳይ ነው – አቶ ሚሊዮን ማቲዎስ

You are currently viewing የመሥሪያ ቦታ አቅርቦት የኢኮኖሚ ፍትህን የማስፈን ጉዳይ ነው – አቶ ሚሊዮን ማቲዎስ

AMN – ሚያዝያ 28/2018 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአስራ አንዱም ክፍለ ከተሞች ለሚገኙ ኢንተርፕራይዞችና አንቀሳቃሾች የመሥሪያ ቦታ ሼዶችን በይፋ አስተላልፏል

በመርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የሥራ እና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሚሊዮን ማቲዎስ ፤ ኢንተርፕራይዞች የከተማዋ የኢኮኖሚ ሞተር እንዲሆኑ ማስቻል ለብልጽግና ጉዞ አማራጭ የሌለው ተግባር ነው ብለዋል፡፡

አቶ ሚሊዮን በንግግራቸው የመሥሪያ ቦታ አቅርቦት ካለው ፋይዳ አንጻር ሲያስረዱ፣ ፍትሃዊ የመሥሪያ ቦታ አቅርቦትን ማረጋገጥ የኢኮኖሚ ፍትህን ከማስፈን ረገድ ከፍተኛ ድርሻ ስላለዉ ይህንኑ ለመተግበር እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ዜጎች ያላቸውን ክህሎትና ጉልበት ወደ ምርት እንዲቀይሩ ለማድረግ መሰረታዊ የሆነውን የመሥሪያ ቦታ ጥያቄ በግልጽነት እና በተጠያቂነት መፍታት ቀዳሚ ተግባር መሆኑንም አብራርተዋል።

ይህ የመሥሪያ ቦታ የማስተላለፍ ሂደት በደንብና በመመሪያ መሰረት ተገምግመው ለቀረቡ፣ በእድገት ተኮር ዘርፎች ለተደራጁ ኢንተርፕራይዞች የተከናወነ መሆኑን ገልጸዉ፤ ሂደቱም ፍጹም ፍትሃዊ በመሆነ አሰራር መከናወኑም ጠቁመዋል፡፡

የመሥሪያ ቦታ የተላለፈላቸው አንቀሳቃሾችም የተሰጣቸውን ዕድል በመጠቀም በቁርጠኝነት እንዲሰሩ አሳስበዋል።

ይህ እርምጃ በከተማዋ የሚታየውን የሥራ አጥነት ችግር ለመቅረፍና ለሥራ ወዳዱ ማህበረሰብ አዲስ የተስፋ ብርሃን ለመፈንጠቅ ያለመ መሆኑም ተመላክቷል።

በፍሬሕይወት ብርሃኑ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review