በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ከተወዳደሩት 42 ፓርቲዎች፣ 17ቱ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መቀመጫ አግኝተዋል

AMN ሰኔ 14/2018 ዓ.ም

ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም በተካሄደው ጠቅላላ ምርጫ ከተወዳደሩት 42 የፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል 17 ፓርቲዎች የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መቀመጫ አግኝተዋል።

ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዛሬ ይፋ ባደረገው የማጠቃለያ ውጤት መሠረት ከ17ቱ የፖለቲካ ፓርቲዎች በተጨማሪ፣ 8 የግል ዕጩዎችም የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ወንበር አሸንፈዋል።

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መቀመጫ ያገኙ የፖለቲካ ፓርቲዎች፦

👉 ብልፅግና ፓርቲ – 438 መቀመጫዎች

👉 የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) – 13 መቀመጫዎች

👉 የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ – 6 መቀመጫዎች

👉 የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ – 3 መቀመጫዎች

👉 የአማራ ዴሞክራሲያዊ ኃይል ንቅናቄ – 3 መቀመጫዎች

👉 ነፃነትና እኩልነት ፓርቲ – 3 መቀመጫዎች

👉 ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት – 2 መቀመጫዎች

👉 የኦጋዴን ብሔራዊ ነፃነት ግንባር – 1 መቀመጫ

👉 ሱማሌ ፌደራሊስት ፓርቲ – 1 መቀመጫ

👉 ኀብረት ለዴሞክራሲና ለነፃነት ፓርቲ – 1 መቀመጫ

👉 የጉሙዝ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ – 1 መቀመጫ

👉 አርጎባ አንድነት ጀበርቲ – 1 መቀመጫ

👉 የአፋር ሕዝብ ፓርቲ – 1 መቀመጫ

👉 አዲስ ትውልድ ፓርቲ – 1 መቀመጫ

👉 ሰላም ለኢትዮጵያ ጥምረት – 1 መቀመጫ

👉 የዎላይታ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ግንባር – 1 መቀመጫ

👉 ጌዴኦ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት – 1 መቀመጫ

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መቀመጫ ያገኙ የግል ዕጩዎች፦

1. በረከት ማርቆስ ደሪሎ

2. አበበ ገመቹ ሌንጫ

3. ቀጀላ መርዳሳ ቱሉ

4. ካሚል ሸምሱ ሲራጅ

5. መለሰ ኢጃራ ደሜ

6. አራርሶ ቢቂላ ኤሌሞ

7. ዲማ ኖጎ ሰርቦ (ዶ/ር)

8. መስፍን ኢልታሞ ኢቻ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review