የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት 1447ኛው የዒድ አለ-አድሃ (ዓረፋ) በዓልን ምክንያት በማድረግ ለሕዝበ ሙስሊሙ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፏል

You are currently viewing የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት 1447ኛው የዒድ አለ-አድሃ (ዓረፋ) በዓልን ምክንያት በማድረግ ለሕዝበ ሙስሊሙ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፏል

AMN ግንቦት 17/2018 ዓ.ም

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የ1447ኛ ውን የዒድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል።

የጠቅላይ ምክር ቤቱ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝደንት ሸይኽ አብዱልከሪም ሸይኽ በድረዲን የእንኳን አደረሳችሁ መልካም ምኞታቸውን ገልፀው ህዝበ ሙስሊሙ በዓሉን በመረዳዳት እና በመተጋገዝ ሊያከብረው እንደሚገባ እና ለሀገር ሰላም ዱዓ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል።

በዓሉ የነቢዩሏህ ኢብራሂም (ዐ.ሰ) ታማኝነት፣ መስዋዕትነትና ትዕግስት የሚታወስበት በመሆኑ ህዝበ ሙስሊሙ መንፈሳዊ እሴቱን ጠብቆ ሊያከብረው እንደሚገባ አስታውሰዋል ።

አቅመ ደካሞችን፣ ወላጅ አልባ ህጻናትንና ህሙማንን በመጠየቅና በመርዳት በዓሉን ማክበር ይገባል ያለው መግለጫው ለሀገር ሰላም እና ለህዝቦች አንድነት መስራት እንደሚገባም ተገልጿል።

የዘንድሮው 1447ኛው የዒድ አል-አድሃ (ዓረፋ) በዓል የፊታችን ረቡዕ ግንቦት 19 ቀን 2018 ዓ.ም እንደሚከበር የፌዴራል ጠቅላይ ሸሪዓ ፍርድ ቤት መግለጹ ይታወቃል።

በመሀመድኑር አሊ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review