ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ያስተላፉት መልዕክት

You are currently viewing ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ያስተላፉት መልዕክት

AMN-ግንቦት 18/2018 ዓ.ም

ብልፅግና ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር እያሸጋገረ ነው።

ባሕር ዳር ደግሞ የዚህ ሕያው ምስክር ናት!

ዛሬ የውቢቷና ታሪካዊቷ የባሕር ዳር ከተማ ሕዝብ ለፓርቲያችን ባደረጉት ደማቅ የድጋፍ ሰልፍ ላይ ታድመናል።

ለባሕር ዳር ነዋሪዎች ስለ ብልፅግና መናገር፤ ለሐዋርያት ስለ ክርስትና፣ ለዑለማዎች ስለ እስልምና እንደማስተማር ነው። ምክንያቱም ባሕር ዳር ራሷ ብልፅግና ሰው ሆኖ የሚንቀሳቀስባት ሕያው ማሳያ ናት!

አዲሱ የዓባይ ድልድይ፣ የኮሪደር ልማት፣ የዓለም አቀፍ ስታዲየም፣ አዲሱ አውሮፕላን ማረፊያ ተርሚናል እና የኢኮ ሪዞርቶች ግንባታና ኢንዱስትሪዎች መስፋፋት በንግግር ሳይሆን በተግባር፣ በብልፅግና ዘመን የተመዘገቡ የባሕር ዳርና የክልላችን እውነታዎች ናቸው።

ለአማራ ክልል ሕዝብ ከብልፅግና ዘመን የተሻለ ዘመን አይመጣለትም። ስለ አማራ ሕዝብ ለዘመናት ሲነዛ የነበረውን የተሳሳተ ትርክት ያረመውና የአማራን ሕዝብ ዕሴቶች ከፍ ያደረገው ብልፅግና ነው።

ፈተናዎቻችን ብዙ ናቸው፤ ዓቅማችንና ቆራጥነታችን ግን ከፈተናዎቻችን በላይ ነው! አማራ በኢትዮጵያ ውስጥ ተገቢውን ቦታ እንዲያገኝ የሚያስችለው፣ ከአማራ ሥነ-ልቦናና ሥሪት ጋር የሚሄደው ብቸኛው ፓርቲ ብልፅግና ነው!

የኢትዮጵያን ትንሳኤና መበልጸግ እውን ለማድረግ ብልፅግናን ይምረጡ!

ምልክታችን የስንዴ ነዶ ነው! የስንዴ ነዶ፤ የጥረት፣ የአንድነትና የሉዓላዊነታችን ተምሳሌት ነው!

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review