የኢድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል የሶላት ሥነ ሥርዓት በስኬት ተጠናቀቀ

AMN ግንቦት 19 ቀን 2018 ዓ/ም

የኢድ አል አድሃ (አረፋ) በዓልን አስመልክቶ የእስልምና እምነት ተከታዮች በአዲስ አበባ ስታዲዮም የሶላት ስነ- ስርዓት አካሂደዋል።

የኃይማኖት አባቶች እና የእምነቱ ተከታዮች፣ የውጭ ሀገር ዜጎች የመንግስት የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት የተካሄደው የሶላት ፕሮግራም በስኬት መጠናቀቁን የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አስታውቋል፡፡

የሶላት ስነ-ስርዓቱ እስከሚጠናቀቅ የትራፊክ መጨናነቅ እንዳያጋጥም ተብሎ ለተሽከርካሪ ዝግ የነበሩ መንገዶቸ መከፈታቸውንም ፖሊስ ገልጿል፡፡

ለፕሮግራሙ ስኬታማነት አስተዋፆኦ ላደረጉ አካላት፣ ኃላፊነታቸውን በአግባቡ ለተወጡ የፀጥታ ተቋማት አመራሮች እና አባላት ፖሊስ ምስጋናዉን አቅርቧል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review