AMN – ግንቦት 24/2018 ዓ.ም
መሰረት አማረ በዓለም ሰላም አካባቢ፣ በወይና ወንዝ አቅራቢያ ትኖራለች፡፡
መሰረት የአንድ ዓመት ከሶስት ወር ህፃን ልጇን በጀርባዋ አዝላ፣ በማለዳ ከጎረቤቶቿ ጋር ወደ ምርጫ ጣቢያ ታመራለች፡፡
ይህ ጉዞ ታዲያ ለተዝናኖት ለአልነበረም፤ የነገዋን ኢትዮጵያ ለመቅረጽ እና ለልጆቿ የተሻለ ህይወትን ለመስጠት የተደረገ የእናትነት ጉዞ እንጂ።
መሰረት ለልጆቿ የተሻለ ሃገር ትመኛለች፤ ለዚህም ምርጫን አስቀድማለች፡፡
ለሷ ምርጫ ማለት የመንግስት ለውጥ ብቻ ሳይሆን፣ የልጆቿ የነገ የትምህርት፣ የጤና እና የሰላም ዋስትና ነው።
በምርጫ ጣቢያው ተገኝታ ድምጿን ለመስጠት ስትሰለፍ የነበረው ድባብ አስደሳችና ተስፋ ሰጪ እንደነበር በፈገግታ ትገልጻለች።
ይቺ ቀን ለአራት እና ለአምስት ዓመታት የሚዘልቅ እጣ ፈንታ የሚወሰንባት ብቸኛ የውሳኔ ቀን መሆኗን የምትረዳው መሰረት፣ በወሰዱት ካርድ እንዲመርጡ በቤታቸው ለቀሩት ወገኖቿ መልዕክት ታስተላልፋለች፦
በታምራት ቢሻው