ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ በሰላም አደባባይ ቁጥር-1 ምርጫ ጣቢያ ድምጻቸውን ሰጡ

AMN ግንቦት 24/2018

የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ በሃዋሳ ምርጫ ክልል ጉዊ ቀበሌ ሰላም አደባባይ ቁጥር-1 ምርጫ ጣቢያ ድምጻቸውን ሰጡ።

ርዕሰ መስተዳድሩ በዚህ ወቅት እንደገለጹት ምርጫ የህዝብ የስልጣን ባቤትነት የሚረጋገጥበት ታሪካዊ ሂደት በመሆኑ ህዝቡ ከማለዳው ጀምሮ ወደ ምርጫ ጣቢያ በመውጣት እየመረጠ ይገኛል።

የድምጽ አሰጣጥ ሂደት ዛሬ ቀኑን ሙሉ እንደሚካሄድ ይታወቃል።

ጠቅላላ ምርጫው 42 የፖለቲካ ፓርቲዎች የሚፎካከሩ ሲሆን ከ54 ሚሊዮን 57 ሺህ በላይ መራጮችም ለመምረጥ ምርጫ ካርድ መውሰዳቸው ይታወቃል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review