ጃፓን ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ አድናቆቷን ገለጸች

AMN ግንቦት 26/2018

በኢትዮጵያ የጃፓን ኤምባሲ ግንቦት 24 የተካሄደውን 7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ ለማደራጀት እና ለመምራት ላደረገው ከፍተኛ ጥረት ለብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አድናቆቱን ገልጿል።

ኤምባሲው ባወጣው ይፋዊ መግለጫ ጃፓን በምርጫ ሂደቱ ላይ ለተሳተፉት እጩ ተወዳዳሪዎች በሙሉ እንዲሁም ድምፃቸውን ለመስጠት ለቻሉ የኢትዮጵያ ዜጎች የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፋለች።

በተጨማሪም ጃፓን የኢትዮጵያን የዲሞክራሲ ሂደት ለመደገፍ ለብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ድጋፍ በማድረጓ የተሰማትን ደስታ ገልጻለች።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review