አሜሪካ አዲስ ታሪክ በመስራት ፓራጓይን አሸነፈች

AMN- ሰኔ 6/2018 ዓ.ም

ከጣምራ አዘጋጆች አንዷ የሆነችው አሜሪካ የ23ኛ ዓለም ዋንጫን ፓራጓይን በማሸነፍ ጀምራለች።

ከ70 ሺ በላይ ተመልካች በሚይዘው ሶፊ ስታዲየም ደመቅ ባለ የመክፈቻ ስነስርዓት የተከናወነውን ጨዋታ አሜሪካ 4ለ1 አሸንፋለች።

የቀድሞ የአርሰናል አጥቂ ፎላሪን ባሎገን ሁለት ግብ ሲያስቆጥር ፣ ጆቫኒ ሬይና እንዲሁም ዳንኤል ቦባዲላ በራሱ ላይ ቀሪ ሁለት ግቦችን አስገኝተዋል። ማውሪሲዮ የፓራጓይን ብቸኛ ግብ አስቆጥሯል።

ለ12ኛ ጊዜ እየተሳተፈች የምትገኘው አሜሪካ በዓለም ዋንጫ አራት ግብ አስቆጥራ ስታሸንፍ በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው።

በማውሪሲዮ ፖቼቲኖ የምትመራው አሜሪካ ምድብ አራትን መምራት ጀምራለች።

ሌላኛዋ አዘጋጅ ሀገር ካናዳ ከቦስኒያ ጋር ተጫውታ 1ለ1 ተለያይታለች።

በቶሮንቶ ስታዲየም በተከናወነው ጨዋታ ጆቮ ሉኪች ለቦስኒያ ክይል ላሪን ለካናዳ ግቦቹን አስቆጥረዋል።

ሦስተኛ ተሳትፎዋን እያደረገች የምትገኘው ካናዳ በዓለም ዋንጫው ለመጀመሪያ ጊዜ ነጥብ አስመዝግባለች። ከዚህ ቀደም ያደረገቻቸውን ስድስት ጨዋታዎች መሸነፏ ይታወሳል።

በሸዋንግዛው ግርማ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review