AMN ሰኔ 17/2018

ለዋናው የሀገራዊ ምክክር ጉባኤ ስምንት አጀንዳዎች መለየታቸውን የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አስታወቀ።
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የዋናው ሀገራዊ ምክክር ጉባኤ ከሐምሌ 8 ቀን 2018 ጀምሮ እንደሚካሄድ ማስታወቁ ይታወሳል።
በዛሬው እለትም የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ለሀገራዊ ምክክር ጉባኤ የሚቀርቡ አጀንዳዎችን ይፋ አድርጓል።
በመርሀ ግብር የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያን ጨምሮ የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽነሮች፣ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ታድመዋል።
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ፥ ኮሚሽኑ ሁሉን አቀፍ ሂደትን በመከተል የተዋጣ ስራ ማከናወኑን ገልጸዋል።
በዚህም ስምንት ሀገራዊ ፋይዳ ያላቸው አጀንዳዎች ተለይተው ለዋናው የምክክር ጉባኤ መለየታቸውን ጠቁመዋል።
ይፋ የተደረጉት ስምንቱ አጀንዳዎች የተቀረጹት ራሰን በቻለ ግልጽ ሥርዓተ መሆኑን ተናግረዋል።
ኮሚሽኑ ላለፉት አራት ዓመታት ሰፊ ዝግጅት ሲያደርግ ቆይቷል፤ በተለያዩ ምዕራፎች ዋናውን ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ ማካሄድ የሚያስችል አሳታፊና አካታች የአጀንዳ ማሰባሰብና ተሳታፊ ልየታ ሥራ ተሰርቷል።
በኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ለዘመናት ሲንከባለሉ የመጡ አለመግባባቶችን በሰለጠነ ምክክር ለመፍታትና ሀገራዊ መግባባት መፍጠር የሚያስችል ምኅዳር ተፈጥሯል።
በኢትዮጵያ በሁሉም ክልሎች፣ ሁለቱ ከተማ አስተዳደሮችና በውጭ ዓለማት ከሚኖሩ ዜጎች ስኬታማ የአጀንዳ ማሰባሰብና ተሳታፊ ልየታ የምክክር መድረክ ተካሂዷል።
የሀገራዊ ምክክሩ የእስካሁን ሂደትም ግልጽ፣ ገለልተኛ፣ አካታችና አሳታፊነቱን ጠብቆ የተካሄደ ነው።