AMN – ሰኔ 28/2018 ዓ.ም
የትውልድ ድምጽ የሆነው አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ከአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ጋር በመተባበር ያዘጋጀው የ“አሸናፊ ትውልድ” የ5 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድር በደመቀ ሁኔታ እየተካሄደ ይገኛል።
መነሻውን ዓድዋ ድል መታሰቢያ ያደረገው ይህ የሩጫ ውድድር ማጠቃለያውን ቀበና የሚያደርግ ይሆናል፡፡

በጎዳና የሩጫ ውድድሩ ላይ የብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ እና የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ሞገስ ባልቻ ፣ የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ሰለሞን ዲባባ ፣ የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አሰግደው ኃይለጊዮርጊስ ፣ የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች፣ የኤ ኤም ኤን አመራር እና ሰራተኞች እንዲሁም የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

ይህ በዓይነቱ ልዩ የሆነው የጎዳና ላይ የሩጫ ውድድር “አሸናፊ ትውልድ” በሚል መሪ ቃል ነው እየተካሄደ ነው የሚገኘው፡፡
በትዝታ መንግስቱ