ሰው አጠፋው፤ ሰው አለማው- ከንቲባ አዳነች አቤቤ

You are currently viewing ሰው አጠፋው፤ ሰው አለማው- ከንቲባ አዳነች አቤቤ

AMN- ሰኔ 22/2018 ዓ.ም

ፈጣሪ የሰጠንን ቀበና “ሰው“ አጠፋው፤ ይህ የተፈጥሮ ስጦታ መጥፋት ቁጭት ያደረበት “ሰው“ ደግሞ ቀበናን ዳግም እንደ አዲስ እንዲወለድ አደረገው ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት መልዕክት፣ የቀበና ወንዝ ለዘመናት በዘፈን እና በትዝታ ብቻ ስሙ ሲነሳና ሲወደስ ኖሮ፣ ዛሬ ግን ዳግም እንዲወለድ አድርጐ አለማው ብለዋል።

አርቲስት ፀሀዬ ዮሀንስ “ቢሻን ቀበና” እያለ ብዙዎች እየዋኙ ያደጉበትን የልጅነት ትዝታን ሲቀሰቅስ፣ የክብር ዶ/ር አርቲስት አሊ ቢራ “ቢሻን አዲስ አበባ“ እያለ ሲያደናንቅ በዘመናት ውስጥ ግን ትዝታን ብቻ ተሸክሞ የወንዙ ተፈጥሯዊ ማንነት ጠፍቶ፣ የፍሳሽ መውረጃና የቆሻሻ መጣያ ሆኖ፣ ጠረኑ አላስጠጋ ብሎ ተረስቶ የኖረ ወንዝ ነበር በማለት አስታውሰዋል።

እነሆ እነዚህ የብክለት፣ የበሽታ ምንጭና የቆሻሻ ማጠራቀሚያ የነበሩትን ወንዞቻችንን ዛሬ ላይ በትጋት እና በላብ እየታከሙ፣ ለነዋሪው ተስፋን ሀሴትን የሚለግሱ የደስታ ምንጭ እየሆኑ ነው ሲሉም አክለዋል፡፡

በአጭር ጊዜ የተገነባው ይህ ድንቅ ፕሮጀክት፣ ከሌሎች የከተማዋ ታላላቅ ፕሮጀክቶች ጋር ተዳምሮ አዲስ አበባን የውበት ማማ አድርጓታል በማለትም ገልጸዋል

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review