AMN ሐምሌ 7/2018 ዓ.ም

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸዉ ባሰፈሩት መልእክት ዛሬ ከከንቲባ ጽ/ቤት አመራሮችና ሰራተኞች ጋር የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ በኤአይ( AI) ዩኒቨርሲቲ አካሂደናል ብለዋል፡፡

“ተስፋን እንትከል” በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ በሚገኘው የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርሃ ግብር በከተማችን 6 ሚሊዮን ችግኞችን ለመትከል አቅደን እየሰራን እንገኛለን ሲሉ ገልጸዋል፡፡

የዘንድሮውን የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ሰኔ 7/2018 ዓ.ም አስጀምረን እስከአሁን 4 ሚሊየን 469 ሺህ 710 ችግኞችን የተከልን ሲሆን፣ አፈፃፀማችንም 75 በመቶ ደርሷል። ችግኝ መትከል ብቻውን ከምናልመው ግብ ስለማያደርሰን የተተከሉ ችግኞችን የመንከባከብ ስራም እንሰራለን ሲሉ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡