ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ ስለ ምክክሩ ሂደት የሰጧቸው ዋና ዋና ነጥቦች

AMN ሐምሌ 11/2018 ዓ.ም

👉 የሀገራዊ ምክክር ሂደቱ ከወረዳ እስከ ፌዴራል፣ እንዲሁም ዲያስፖራውና ዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ በተገኙበት በደማቅ ሁኔታ ተጀምሯል።

👉 ምክክር እንደ ተለመደው የፖለቲካ ክርክር ወይም በአብላጫ ድምፅ የሚወሰን ሳይሆን፣ በጋራ መግባባት ላይ የሚደረስበት ታሪካዊ ሂደት ነው።

👉 4 ሺህ ተሳታፊዎች ለስምንቱ አጀንዳዎች ዝርዝር ማብራሪያና የውሳኔ አሰጣጥ ስነ-ዘዴዎች ላይ ስልጠና ወስደዋል።

👉 ሂደቱ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች፣ ክልሎች ሳይቀሩ እኩል ድምፅና መስተጋብር እንዲኖራቸው ታሳቢ ተደርጎ የተዘጋጀ ነው።

👉 በሂደቱ መሳተፍ የሚፈልጉ ተጨማሪ የፖለቲካ ፓርቲዎችና ታጣቂዎች አሁንም በሩ ክፍት መሆኑን ኮሚሽነሩ ገልጸዋል።

👉 ቅዳሜና እሁድ የነበሩ ጥቃቅን የአደረጃጀት ክፍተቶች ተስተካክለው፣ ከሰኞ ጀምሮ ሙሉ አቅም ያለው የቡድን ውይይቶች ይጀምራሉ።

👉 የሚዲያ አካላት ሂደቱን በየክልሉ በሚነገሩ ቋንቋዎች ለህዝቡ በማድረስ ረገድ ያላቸው ሚና ከፍተኛ መሆኑን አሳስበዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review