አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ የላቀ አፈጻጸም በማስመዝገብ እውቅና ተሰጠው

AMN- ሐምሌ 12/2018 ዓ.ም

የትውልድ ድምጽ የሆነው አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ በ2018 በጀት ዓመት የላቀ አፈጻጸም በማስመዘግቡ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እውቅና ተበርክቶለታል፡፡

የ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት እቅድ አፈጻጸምን መሠረት በማድረግ በተካሄደው ከተማ አቀፍ ምዘና ተቋሙ ከፍተኛ ውጤት በማስመዝገቡ ነው የእውቅና ምስክር ወረቀት የተበረከተለት፡፡

የእውቅና ምስክር ወረቀቱን ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ የተቀበሉት የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ሰለሞን ዲባባ ናቸው፡፡

አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ የከተማዋን የልማትና መልካም አስተዳደር ስራዎች ሽፋን በመስጠት ገንቢ ሚናውን እየተወጣ ይገኛል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review