AMN- ጳጉሜን 03/ 2018 ዓ.ም

መዲናችን አዲስ አበባ የአየር ንብረት ለውጥን በመቋቋም ከአፍሪካ ቀዳሚ ፣ ከዓለም 2ኛ ከተማ መሆኗን የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ፡፡
ከንቲባ አዳነች በማህበራዊ የትስስር ገፃቸው ባስተላለፉት መልዕክት እንደገለደጹት ዘኒዮርክ ታይምስ (The New York Times) ይዞት በወጣው ዘገባ፣ የቦታዎች ስጋት የሚያጠናና የሚተነብይ (AlphaGeo) ጂኦስፓሻል ኩባንያ በዓለም ላይ ካሉ ትልልቅ ከተሞች የ72 ቱን የአየር ንብረት የመቋቋም አቅም (Resilience) ደረጃ መድቧል ብለዋል።

በዚህ መሠረት የተቀመጠውን መስፈርት በሟሟላት፣ ከተማችን አዲስ አበባ ከአፍሪካ ቀዳሚ ከዓለም ሁለተኛ ከተማ ሆና ተቀምጣለች ብለዋል ከንቲባ አዳነች አቤቤ።
ከንቲባዋ አክለውም ከተማችን አዲስ አበባ እንደስሟ ውብ፣ ንፁህ እና ለመኖር ምቹ ከተማ እናደርጋለን ብለን በገባነው ቃል መሠረት፣ የአፍሪካ ኩራት በአጭር ጊዜ የከተማ ልማት ለውጥ ተምሳሌት በመሆን ላይ ነች ነው ያሉት።
ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለመላዉ የከተማችን ነዋሪዎች እና አብራችሁን ተባብራችሁ የሰራችሁ ሁሉ እንኳን ደስ አላችሁ በማለት በመልዕክታቸው የተሰማቸውን ደስታ ገልጸዋል።