ወጣቶች በማህበራዊ አገልግሎት ላይ በንቃት እንዲሳተፉ ለማድረግ በከተማዋ የሚገኙ የስብዕና መገንቢያ ማዕከላት ሚና ከፍተኛ ነው

AMN – ሐምሌ 16/2018 ዓ.ም

ወጣቶች በማህበራዊ አገልግሎት ላይ በንቃት እንዲሳተፉ ለማድረግ በከተማዋ የሚገኙ 114 የስብዕና መገንቢያ ማዕከላት ሚና ከፍተኛ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ገለጸ፡፡

በየካ ክፍል ከተማ ወረዳ 7 የወጣት ስብዕና መገንቢያ ማዕከል የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ማስጀመሪያ መድረክ ተካሂዷል።

በዚሁ ወቅት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ ክብር ዓለም ደምሴ፤ እንደ ሀገር የተያዘውን የ7 ሚሊየን ኮደርስ ስልጠና ከግብ ለማድረስ በክረምቱ በርካታ ስራዎች ይከናወናሉ ብለዋል፡፡

ወጣቶችን በበጎ ስብዕና ለማነጽ በማህበራዊ አገልግሎት ላይ በንቃት እንዲሳተፉ ለማድረግ በከተማዋ የሚገኙ 114 የስብዕና መገንቢያ ማዕከላት ሚና ከፍተኛ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በወጣት ስብዕና መገንቢያ ማዕከላት የክረምት ወቅት መደበኛ የበጎ ፍቃድ አገልግሎት በትኩረት እየተሰራ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

ለዚህም የወጣቶች ስብዕና መገንቢያ ማዕከላቱ ለክረምቱ ዝግጁ መሆናቸውን ጠቁመዋል።

በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት አበይት ስራ በሆነው የደም ልገሳ መርሐ ግብር በ1 ቀን 1 ሺህ ዩኒት ደም መሰብሰብ እንደተቻለም አንስተዋል።

በቀጣይ የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ስራው ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ተገልጿል።

በወንድምአገኝ አበበ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review