በተመራማሪዎችና በፖሊሲ አውጪዎች መካከል የተናጠል አሠራርን በማስወገድ የፖሊሲ ጥናቶች በጋራ እንዲቀረጹ ማድረግ ያስፈልጋል

You are currently viewing በተመራማሪዎችና በፖሊሲ አውጪዎች መካከል የተናጠል አሠራርን በማስወገድ የፖሊሲ ጥናቶች በጋራ እንዲቀረጹ ማድረግ ያስፈልጋል

AMN ሐምሌ 15/2018

የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት ፖሊሲ አውጭዎች እና ተመራማሪዎች ፖሊሲን በማውጣት እረገድ ማስረጃን መጠቀም በሚችሉባቸው ጉዳዮች ላይ ከተለያዩ ዓለም አቀፍ የምርምር ተቋማት ጋር የውይይት መድረክ አካሂዷል፡፡

በውይይቱ ላይም በተመራማሪዎችና በፖሊሲ አውጪዎች መካከል ያለውን ክፍተት ማጥበብ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ምክክር ተደርጓል፡፡

የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ፍቃዱ ፀጋ በዚሁ ወቅት፤ እንደሀገር ተቋማት ጥናትን መሠረት ያደረጉ ሥራዎች መሥራታቸው ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ በመምጣቱ ለውጦች እየተመዘገቡ ነው ብለዋል፡፡

ተቋማቸው በኢትዮጵያ በማስረጃ ላይ የተመሠረቱ በየዓመቱ በአማካይ ከ40 እስከ 60 የሚሆኑ ጥናትና ምርምሮችን ለተጠቃሚዎች ተደራሽ እንደሚያደርግም አስታውቀዋል፡፡

ጥናትና ምርምሮችን ውጤታማ ለማድረግ በተመራማሪዎችና በፖሊሲ አውጪዎች መካከል ያለውን የተናጠል አሠራር በማስወገድ የፖሊሲ ጥናቶች ከጅምሩ በጋራ እንዲቀረጹ ማድረግ ያስፈልጋልም ተብሏል፡፡

የፖሊሲ ዐውደ ጥናቶች በግብርና፣ በጤና፣ በትምህርትና በማኅበራዊ ደኅንነት ዙሪያ የሚተገበሩ ፖሊሲዎችና ፕሮግራሞች ያመጡትን ቀጥተኛ ለውጥ በሳይንሳዊ መንገድ በመለካት የሀብት ብክነትን ማስቀረት እንደሚገባም ተመላክቷል።

የምርምር ውጤቶች በቀጥታ ለሀገር ልማትና ለሕዝብ ጥቅም እንዲውሉ የጋራ ጥናትና የተፅዕኖ ግምገማዎችን ማካሄድ አስፈላጊ መሆኑም ተጠቅሷል፡፡

በደሳለኝ ሙሐመድ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review