
ዛሬ ሀገር በቀል ሆኖ በሰባት አምዶች ተደራጅቶ የተቀረጸውን የመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር አፈጻጸም ሪፖርት ለሪፎርም ምክር ቤቱ ቀርቦ በዝርዝር ተገምግሟል።
አምዶቹም ዘመኑን የዋጀና በተዋረድ የተናበበ አደረጃጀት፣ ብቃት ያለው የሰው ኃይል ስምሪት፣ ብዝሃነት፣ ዲጂታላይዜሽ፣ የለውጥ አመራር እና የአገልግሎት ማሻሻያን የያዘ ነው።

አፈጻጸሙም ፍጥነትን፣ ፈጠራን፣ ፈጻሚዎቹን ባለቤት ማድረግንና ዘላቂ ሥርዓት ግንባታን መሠረት ተደርጎ በጥብቅ ዲስፕሊንና በእውቀት ውጤታማ እና ተስፋ በሚሰጥ ሁኔታ እየተፈጸመ መሆኑንም አይተናል።

በሪፖርቱ ሰው ተኮር በሆነ ሁኔታ የመሶብ አገልግሎት በማስፋፋት ሂደት ጉልህ የሚባል መሻሻል በየከተሞቹ ታይቷል። በአገልግሎት ማሻሻያ ረገድ ትልቅ ለውጥ ማምጣት የምንችል መሆኑንና በዜጎች በኩል የነበረውን እሮሮ መፍታት መጀመራችን በተግባር የታየበትም ጉዳይ ነው።

የተጀመረው የመንግስት አገልግሎት ማሻሻያ በቴክኖሎጂ፣ በፍጥነት፣ በፈጠራ፣ በጥራትና በታማኝነት ማስፋፋቱ ተጠናክሮ መቀጠል ይኖርበታል። ለዚህም ሥራ የጠራ መረጃ ማደራጀት፣ ቴክኖሎጂን ማበልጸግ እና የሰራተኞችን ብቃት ማጠናክር የቀጣይ ትኩረት እንዲሆን በምክር ቤቱ አቅጣጫ ተቀምጧል።