የታሪክ ትርክትን ማደስ ያስፈልጋል – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

AMN ሐምሌ 25/2018 ዓ.ም

የወደፊቷን ኢትዮጵያ ለማጽናት ብሎም በሕዝቦች መካከል ያሉ ታሪካዊ ዕሴቶችን እና የጋራ ውኅደቶችን ያጎለበተ አዲስ የታሪክ ትርክት መገንባት እንደሚያስፈልግ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አስገነዘቡ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ጋር ባደረጉት ቆይታ፤ የኢትዮጵያ ሕዝቦች ታሪክ በግጭት ሳይሆን በዘመናት መካከል በነበሩ ሰፋፊ የፖለቲካ ዳይናሲቲዎች፣ የንግድ መስመሮች እና ባሕላዊ ትስስሮች የተገነባ መሆኑን አብራርተዋል፡፡

አክለውም፤ በአማራ እና በኦሮሞ ሕዝቦች መካከል ለዘመናት የዘለቀው ግንኙነት በፖለቲካዊ ሴራ ሳይሆን በጋብቻ፣ በጉዲፈቻ፣ በጋራ ተጋድሎ እና በተፈጥሯዊ መዋኀድ ላይ የተመሠረተ መሆኑን ጠቅሰዋል።

ዳግማዊ አጼ ምኒልክ ያለ ጎበና፣ ጎበናም ያለ ዳግማዊ አጼ ምኒልክ ዘመናዊቷን ኢትዮጵያ መፍጠር የሚችሉበት ምንም አይነት እድል እንዳልበረም አውስተዋል፡፡

እንደ ዓድዋ ያሉ ሀገራዊ ድሎች የተገኙት በሕዝቦች የጋራ ውኅደት እና በከፈሉት መስዋዕትነት የተገኙ ውጤቶች መሆናቸውንም አስገንዝበዋል፡፡

በሕዝቦች መካከል ያለውን የመለያየት ግድግዳ በማፍረስ፣ በጋራ እምነቶች እና ዕሴቶች ላይ ያተኮረ የመደመር መንገድን መከተል ብቸኛው ሀገርን የማጽናት አማራጭ መሆኑንም ነው ያስገነዘቡት፡፡

በወርቅነህ አቢዮየታሪክ ትርክትን ማደስ ያስፈልጋል – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

በወርቅነህ አቢዮ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review