አረንጓዴ አሻራ የጋራ ስኬት የትውልድ ተስፋ እና የማይደበዝዝ አሻራ ነው- አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ

You are currently viewing አረንጓዴ አሻራ የጋራ ስኬት የትውልድ ተስፋ እና የማይደበዝዝ አሻራ ነው- አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ

AMN – ሐምሌ 27/2018 ዓ/ም

ተስፋን እንትከል በሚል መሪ ሀሳብ እንደ ሀገር 800 ሚሊዮን ችግኞችን በአንድ ጀምበር የመትከል ንቅናቄ በመላ ሀገሪቱ እየተከወነ ነው፡፡

የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ተገኝተው የአረንጓዴ አሻራቸውን አሳርፈዋል፡፡

የአረንጓዴ አሻራ የጋራ ስኬት የትዉልድ ተስፋ እና የማይደበዝዝ አሻራ ነዉ ያሉት አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ፣ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ተፈጥሮን ከሰዉ ልጅ ጋር ያስታረቀ ሀገር በዓለም መዝገብ ስሟን በወርቅ ቀለም የፃፈችበት ነው ብለዋል፡፡

በአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ምድርን አረንጓዴ የማልበስ እና የምግብ ሉዐላዊነትን የማረጋገጥ ጉዞ በስኬት የታጀበ ነው ብለዋል፡፡

በችግኝ ተከላው ላይ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች እየተሳተፉ ነው፡፡

በተመስገን ይመር

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review