AMN- ነሐሴ 8/2018 ዓ.ም

የኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ የድህረ ምረቃ ተማሪዎች እና የዩኒቨርሲቲው ምሁራንን ያካተተ የልዑካን ቡድን በአዲስ አበባ የተለያዩ የቱሪዝም መዳረሻዎችን ጎብኝተዋል፡፡

የልዑካን ቡድኑ የአብርሆት ቤተ-መጻሕፍት፣ የሳይንስ ሙዚየም፣ የአራዳ ፓርክ፣ የወንዝ ዳር ልማት እና የአንድነት ፓርክን ተመልክተዋል፡፡

በጉብኝታቸው ባዩት የቱሪዝም ሀብት እና በአዲስ አበባ ፈጣን የልማት ጉዞ እጅግ መደነቃቸውን እንደገለጹም የአዲስ አበባ ቱሪዝም ኮሚሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

አዲስ አበባ በሚኖራቸው ቆይታም በከተማዋ የሚገኙ ሌሎች የቱሪዝም መዳረሻዎችንና የልማት ስራዎችን የሚጎበኙ ሲሆን ጉብኝቱ የከተማዋን የቱሪዝም ሀብት በዓለም አቀፍ ደረጃ ለማስተዋወቅ፣ የቱሪዝም ኢንቨስትመንት ዕድሎችን ለማስፋት እና የጋራ ትብብርን ለማጠናከር ትልቅ አስተዋጽኦ ይኖረዋል።