AMN- ነሐሴ 10/2018 ዓ.ም

ለአንድ ወር ሲካሄድ የቆየውና 24 ክለቦች የተሳተፉበት የአዲስ አበባ ጨፌ ሜዳ የክረምት እግር ኳስ ውድድር ዛሬ ፍጻሜውን ያገኛል፡፡
ሽሮ ሜዳ እና ስታዲየም ዙሪያ ክለቦች ለዋንጫ እየተፋለሙ ይገኛሉ፡፡

ዋንጫውን የሚያሸንፈው ክለብ የአንድ ሚሊየን ብር ሽልማት እንደሚበረከትለት ተገልጿል፡፡
ውድድሩን የአዲስ አበባ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ከቤላ ስፖርት ጋር በመተባበር አዘጋጅተውታል፡፡
