AMN- ነሐሴ 12/2018 ዓ.ም
አዲስ ሚዲያ ኔትወርክ ሀገራዊ ጉዳዮች እና ንቅናቄዎች በተግባር ይገለጡ ዘንድ ለህዝብ ግንዛቤ ከመፍጠር ባለፈ፣ በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ግንባር ቀደም ተሳትፎ እያደረገ መሆኑ ተገለጸ።
የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ እና የቴሌቪዥን ዘርፍ ኃላፊ አቶ ጥላሁን ካሳ፣ ተቋሙ ታሪክን ከመንገር፣ የዛሬ ልማትን ከማብሰር እና ነገን ከመተንበይ ባሻገር በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ሁልጊዜም ግንባር ቀደም መሆኑን ገልጸዋል።
ተቋሙ ማህበራዊ ኃላፊነትን በተግባር በማረጋገጥ እና በሀገራዊ የጋራ አጀንዳዎች ላይ በንቃት በመሳተፍ የሚታወቅ ሲሆን፣ በሀገር አቀፍ የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ያለፉት ዓመታት ስኬቶች ውስጥ የህዝብን ተነሳሽነት በማላቅ፣ ግንዛቤ በመፍጠር እና በመስክ በመገኘት ደማቅ አሻራውን አሳርፏል።
በሁለት የቴሌቪዥን ቻናሎች፣ በሬዲዮ፣ በጋዜጣ እንዲሁም በዲጂታል ሚዲያ አማራጮች ፍጥነት፣ ጥራት እና ፈጠራን ያቀናጁ መረጃዎችን ለህዝብ እያደረሰ ይገኛል።
የአዲስ አበባ ከተማ አንደበት፣ የልማት አብሳሪ እና የህዝብና መንግስት አገናኝ ድልድይ በመሆን ኃላፊነቱን እየተወጣ ይገኛል።
ባለፉት ዓመታት በአረንጓዴ አሻራ ንቅናቄ የችግኝ ተከላ ላይ የተቋሙ አመራሮች እና ሰራተኞች የነቃ ተሳትፎ ያደረጉ መሆኑን አቶ ጥላሁን አስታውሰዋል።

ሚዲያው በሀገር የሚመዘገቡ ስኬቶችን ከመዘገብ ባለፈ የሀገራዊ ስኬቶች ተቋዳሽ እና የታሪክ አካል እየሆነ መምጣቱን ገልጸዋል፡፡
በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ተቋሙ እና ሰራተኞቹ ግንባር ቀደም ሆኖ እንደሚገኙ የገለጹት ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚው፣ የተከናወነው የችግኝ ተከላም ሀገራዊ የጋራ ጉዳይን በጋራ ለማሳካት የተደረገ መሆኑን ጠቁመዋል።
በቀጣይም የተተከሉ ችግኞች በአግባቡ ጸድቀው ውጤት እንዲያመጡ በትኩረት እንደሚሰራ ተናግረዋል።
በተመስገን ይመር