በከተማዋ የመብራት መሰረተ ልማት መሟላት የምሽት ንግድ እንቅስቃሴ እንዲነቃቃ አድርጓል

AMN- ነሐሴ 12/2018 ዓ.ም

በ2018 በጀት ዓመት የከተማዋን ዘመናዊ የመብራት መሰረተ ልማት ሽፋን ማሳደግ እንደተቻለ የአዲስ አበባ ከተማ የመብራት አገልግሎት አስተዳደር ባለስልጣን አስታውቋል።

ባለስልጣኑ የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም እና የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድን አስመልክቶ ከባለድርሻ አካላት ጋር የውይይት መድረክ አካሂዷል።

በመድረኩ እንደተገለጸው፤ ከ41 ሺህ በላይ የከተማዋ የመብራት መሰረተ ልማቶች በመረጃ ዲጂታላይዜሽን እና በጂኦግራፊያዊ መረጃ መሰረተ ልማት (GIS) ስርዓት ውስጥ እንዲካተቱ ተደርጓል፡፡

እንዲሁም በበጀት ዓመቱ ከ14 ሺህ በላይ የመብራት ፖሎች የጥገና ሥራ ተከናውኗል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ መብራት አገልግሎት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሰብስብ ሁሴን (ዶ/ር) እንዳሉት፤ በ9101 ነጻ የስልክ ጥሪ እና በሌሎች አማራጮች ከማህበረሰቡ የሚነሱ የመብራት መሰረተ ልማት ጥገና ጥያቄዎች ላይ ፈጣን ምላሽ እየተሰጠ ይገኛል።

የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ሥራ አስኪያጅ ተፈራ ሞላ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ በከተማዋ የመብራት መሰረተ ልማቶች መሟላት ለመዲናዋ የምሽት የንግድ እንቅስቃሴ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከቱን ገልጸዋል።

መሰረተ ልማቱ ጨለማን ተገን በማድረግ የሚፈጸሙ ወንጀሎችን በመከላከል እና የምሽት የንግድ እንቅስቃሴ ስኬታማ እንዲሆን በማድረግ ረገድ ጉልህ ሚና አበርክተዋል፡፡

በመድረኩ ባለስልጣኑ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በጋራ መሥራት የሚያስችለውን የመግባቢያ ሰነድ ስምምነትም ተፈራርሟል።

በዳንኤል መላኩ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review