AMN – ነሐሴ 13/2018 ዓ.ም
ዓለም አቀፍ የልማት አጋሮች ልዑካን ቡድን የሀገራዊ ምክክር ጉባኤውን አሁናዊ ሂደት ተዘዋውሮ ተመለከተ፡፡
በተባበሩት መንግስታት የልማት ድርጅት (UNDP) እና በኢፌዲሪ የገንዘብ ሚኒስቴር አስተባባሪነት የተመራውና ለኮሚሽኑ ልዩ ልዩ ድጋፎችን የሚያደርጉ የልዩ ልዩ ሀገራት ወኪሎችን ያቀፈው የልዑካን ቡድን አባላት በምክክሩ ቦታ በአካል በመገኘት ሂደቱን ተዘዋውረው ተመልክተዋል።

የልዑካን ቡድኑ አባላት ካደረጉት የመስክ ጉብኝት በተጨማሪ፣ የሀገራዊ ምክክር ጉባኤውን አጠቃላይ ሂደትና እስከ አሁን የተከናወኑ ዐበይት ተግባራትን አስመልክቶ በኮሚሽኑ ኮሚሽነሮች አማካኝነት ዝርዝር ገለፃ እንደተደረገላቸው የኮሚሽኑ መረጃ ያመላክታል።