AMN- ነሐሴ 16/2018 ዓ.ም.

የኦሮሚያ ልማት ማህበር በህዝብ የተቋቋመ እና ለህዝብ ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት የሚሰራ መሆኑን የኦሮሚያ ክልል የቀድሞ ፕሬዚዳንት እና የኦሮሚያ ልማት ማህበር የቦርድ ሰብሳቢ አቶ አባዱላ ገመዳ ተናገሩ፡፡

የኦሮሚያ ልማት ማህበር የ2018 በጀት ዓመት አፈፃፀሙን እና የ2019 በጀት ዓመት እቅዱን ገምግሟል፡፡
የኦሮሚያ ክልል የቀድሞ ፕሬዚዳንት እና የኦሮሚያ ልማት ማህበር የቦርድ ሰብሳቢ አቶ አባዱላ ገመዳ፣ የኦሮሚያ ልማት ማህበር በክልሉ የተለያዩ መሰረተ ልማቶችን በማስፋት ለህዝቡ ተጠቃሚነት ሁለንተናዊ አሻራውን እያሳረፈ ነው ብለዋል፡፡

ኦልማ የህዝብ ሀብት የሆነ ለህዝቡም የሚሰራ ነው ያሉት አቶ አባዱላ፣ ህብረተሰቡ ለማህበሩ ያላሳለሰ ድጋፋን አጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል፡፡
ማህበሩ በትምህርት ዘርፉ ከክልል የተሻገረ ለሀገር የሚጠቅሙ አለፍ ሲልም በዓለም አቀፍ ደረጃ ስመጥር ዜጎችን እያፈራ እንደሚገኝ በማንሳት፣ በጤና እና ሌሎች መሰረተ ልማት ግንባታዎች ላይ በንቃት ይሳተፋል ብለዋል፡፡
ማህበሩ የተሻለ አፈጻጸም ላላቸው እና ለማህበሩ ሁለንተናዊ ድጋፍ ላደረጉ አካላት እውቅና እና ሽልማት ሰጥቷል፡፡
በተመስገን ይመር