AMN- ነሐሴ 30/2018 ዓ.ም
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሰራተኞች በአዲስ አበባ ከአንጦጦ መቀጠያ እስከ ፒኮክ ፓርክ ድረስ የተሰሩትን የወንዝ ዳርቻ ልማትን ጉብኝተዋል::
ሰራተኞቹ የመዲናዋን አዲስ ገጽታና የቱሪዝም ሳቢነት የሚያጎሉ የመሰረተ ልማት እና የአካባቢ ጥበቃ ስራዎችን ተመልከተዋል።
በጉብኝታቸውም በመዲናዋ የተከናወኑት የልማት ስራዎች እጅግ የሚደነቁ መሆናቸውን ጠቁመው፣ አዲስ አበባን የአፍሪካ የቱሪዝም ማዕከል ለማድረግ የተጀመረውን ሁሉን አቀፍ የልማት ስራ እንደሚደግፉ እና የድርሻቸውን ለመወጣት እንደሚሰሩ ማረጋገጣቸውን ከከንቲባ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
የአዲስ አበባ ቱሪዝም ኮሚሽን በከተማዋ የሚገኙ የተለያዩ ተቋማት ሰራተኞች በመዲናዋ የለሙትን የቱሪዝም መዳረሻዎች እንዲጎበኙ በርካታ የማስተዋወቅ ስራን እያከናወነ ይገኛል::