የማንሰራራት ቀንን ምክንያት በማድረግ የሳይክል እና የስኬት ፌስቲቫል እየተካሄደ ነዉ

AMN-ጳጉሜን 2 /2018 ዓ.ም

የማንሰራራት ቀን አዲስ አበበን ጨምሮ በሃገር አቀፍ ደረጃ በተለያዩ መርሃ ግብሮች እየተከበረ ይገኛል።

ቀኑን ምክንያት በማድረግ በመዲናዋ የሳይክል እና የስኬት ፌስቲቫል በመካሄድ ላይ ይገኛል።

በአዲስ ፓርክ እየተካሄደ በሚገኘዉ በዚህ ፌስቲቫል ላይ በርካታ ስፖርተኞች እና የከተማዋ ነዋሪዎች ተገኝተዋል።

ስፖርታዊ ፌስቲቫሉ ህብረተሰቡ የአካል ብቃት እንቅስቃሴን ባህል እንዲያደርግ ከማስቻሉ ባሻገር ፣ ለአካባቢ ጥበቃ እና ለአየር ንብረት ንፅህና ተስማሚ የሆኑ የትራንስፖርት አማራጮችን ለማስፋፋትና የወጣቶችን የስፖርት ተሳታፊነት ለማሳደግ ታልሞ የተዘጋጀ መሆኑን የአዲስ አበባ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ መረጃ ያመላክታል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review